ስለእርስዎ እናስባለን። እንታገላለን። እናሸንፋለን።

የሕግ ጉዳዮች ምን ያህል አስጨናቂ እንደሆኑ እንረዳለን። ለዛም ነው ያለንን የሙያዊ ችሎታ ተጠቅመን በእያንዳንዱ መንግዶ ላይ ልናግዞ የተዘጋጀነው። ጉዳት ደርሶቦት ፍትህ እየፈለጉ ሆነ፣ የወደፊት እቅድን ለማውጣት ወይም የንግድ ስራ ፍላጎቶችዎን ለማስጠበቅ፣ ህጋዊ አላማዎችዎን በልበ ሙሉነት እንዲሳኩ ለማገዝ ቁርጠኞች ነን። ለፍትህ ባለን አቋም አንደራደርም።

ለነፃ ምክር ቀጠሮ ይያዙ

ለምን እኛን ይምረጡ?

  • የደንበኛ እርካታ

    ዋናው የህግ ቢሯችን ተግባራችን እያንዳንዱ ደንበኛ በሰጠነው ጥብቅና መደሰቱ ነው። በቀናነት የተሞላ የጥብቅንና አገልግሎት ለመቅረብ ቆርጠን ተነስተናል።

  • ግልጽነት

    ለእያንዳንዱ ደንበኛ ጊዜ ዋጋ እንሰጣለን በጊዜ መረጃዎን ማግኘት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ስለምንረዳ የእያንዳንዱ የጉዳይዎ እርምጃ እናሳውቆታለን።

  • ማህበረሰብ-ተኮር

    ከደንበኞቻችን ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነትን በመገንባት እናምናለን፣ ከኛ ጋር ሲሰሩ፣ ለማገልገል ከተወሰነ የህግ ቢሮ ጋር እየሰሩ እንደሆነ ያስታውሱ።

በአደጋ ወይም በሌላ ሰው ቸልተኛነት ምክንያት አካላዊ እና ስሜታዊ ጉዳት እና የገንዘብ ኪሳራ የደረሰባቸውን ቴክሳስ ውስጥ የሚገኙ ደምበኞችን እንወክላለን። ዋነኛ አላማችን ደንበኞቻችን ከደረሰባቸው ጉዳት ለማገገም እና ህይወታቸውን ለማራመድ የሚያስፈልጋቸውን እንክብካቤ፣ ድጋፍ እና ማካካሻ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ነው።

አደጋ

ለአካላዊ ጉዳቶ ካሳ ይገባዎታል

ለስሜታዊ ጉዳቶ ካሳ ይገባዎታል

ለገንዘቦ ኪሳራ ካሳ ይገባዎታል

ለመኪናዎ ጉዳት ካሳ ይገባዎታል

ለጠፋ የስራ ገቢዎ ካሳ ይገባዎታል

ለአዕምሮ ጉዳቶ ካሳ ይገባዎታል

ለአካላዊ ጉዳቶ ካሳ ይገባዎታል ⋆ ለስሜታዊ ጉዳቶ ካሳ ይገባዎታል ⋆ ለገንዘቦ ኪሳራ ካሳ ይገባዎታል ⋆ ለመኪናዎ ጉዳት ካሳ ይገባዎታል ⋆ ለጠፋ የስራ ገቢዎ ካሳ ይገባዎታል ⋆ ለአዕምሮ ጉዳቶ ካሳ ይገባዎታል ⋆

የውርስ እቅድ  እና 

የፍርድ ቤት ክፍፍል

በውርስ እና በንብረት እቅድ አገልግሎታችን ስር እንደ ኑዛዜ፣ አደራዎች፣ የውክልና ሥልጣን እና የቅድሚያ መመሪያዎች ያሉ ህጋዊ ሰነዶችን በማዘጋጀት ከደንበኞች ጋር በቅርበት እንሰራለን። ደንበኞቻችን ለጡረታ እቅድ ሆነ፣ የቤተሰቦቻቸውን የወደፊት የፋይናንስ ሁኔታ ለመጠበቅ ወይም ውስብስብ የሆነውን የአረጋውያን እንክብካቤን ለመከታተል፣ የእኛ ባለሙያዎች ጥሩ ምክር እና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

የውርስ እና ንብረት እቅድ ማውጣት

በህግ ቢሯችን የፍርድ ቤት ውርስ ክፍፍል ወይም የሟችን የውርስ ፈቃድ የማፅደቅ እና ንብረቶቻቸውን በኑዛዜው ወይም በግዛቱ ህግ መሰረት የማከፋፈል ህጋዊ ሂደትን ተከታትለን እናስፈጽማለን። ቀጥተኛ የፍርድ ጉዳይ ይሁን የተወሳሰበ የንብረት አስተዳደር ጉዳይ የህግ ቢሯችን ቁርጠኛ ቡድን በግል መድቦ ትኩረት በመስጠት እና ለደንበኞቻችን የተሻለውን ውጤት ለማግኘት ይሰራል።

የፍርድ ቤት ውርስ ክፍፍል     

ደንበኞቻችን ስለእኛ ምን ይላሉ?

የህግ ቢሯችንን ያግኙ

እርሶ በጉዳዮ ላይ ማተኮር እንዲችሉ የህግ ጉዳዮን ለኛ ይተውልን።

የህግ ቢሯችን መስራች እና ማኔጂንግ ጠበቃ

ሩቲ በላቸው የህግ ቢሯችን መስራች እና ማኔጂንግ ጠበቃ ስትሆን የግል ጉዳት ሰለባ ለሆኑ ፣ የቤተሰብን ውርስ ማስጠበቅ ለሚፈልጉ እና በአነስተኛ የንግድ ሥራ ለተሰማሩ ባለቤቶች ጥብቅና መቆም እና ማገዝ ዋነኛ አላማዋ ነው።

ሩቲ በአሪዞና ዩኒቨርሲቲ ከጄምስ ኢ ሮጀርስ የህግ ትምህርት ቤት (James E. Rogers Law School) የJuris Doctorate ሰርታለች። በJames E. Rogers ቆይታዋም የቢዝነስ ሙግት (Business Litigation ) እንዲሁም የግብይት ንግድ ህግ(Transactional Business Law ) ሰርተፍኬቶችን ተሸልማለች። ሩቲ በአሪዞና ውስጥ አሉ ከሚባሉ የህግ ቢሮች ፣ ከቺካጎ ከተማ የህግ ዲፓርትመንት እና ከዳኛ ማርጋሬት ጆንስ-ጆንሰን ጋር በዳላስ ፕሮቤት ፍርድ ቤት ሠርታለች። ከዚህ በተጨማሪም ለዩኤስ ዲፓርትመንት የአገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ የመሬት አስተዳደር እንዲሁም የቱክሰን ዝቅተኛ ገቢ ግብር ከፋይ ክሊኒክ በጎ ፈቃደኝነት አገልግላለች።

ሩቲ በግል ጉዳት፣ በንግድ ህግ እና በኢስቴት እቅድ ላይ ታተኩራለች። በመቶዎች የሚቆጠሩ የተጎዱ ደንበኞች ተገቢውን ኢንሹራንስ እንዲያገኙም ወክላለች። በግሏ የህግ ቢሮ ከመክፈቷ በፊት፣ ከዩኤስ የሰራተኛ ክፍል OWCP የፌደራል ሰራተኞችን ለሰራተኛ ካሳ ጥያቄያቸው ተገቢውን ካሳ እንዲያገኝ ወክላለች።

ሩቲ በቴክሳስ ግዛት ውስጥ ህግ ጥብቅና ፈቃድ ያላት ሲሆን ለሁለት ተከታታይ አመታትም (2023 እና 2024) በሱፐር ጠበቃዎች የቴክሳስ ራይዚንግ ስታር ተባለች። ሩቲ አማርኛን አቀላጥፋ የምትናገር ሲሆን ነፃ ጊዜዋን ከቤተሰብ እና ከጓደኞቿ ጋር ታሳልፋለች። የተለያዩ ባህሎችን ማየት እና መጓዝም ትወዳለች።

ሩቲ በላቸው

የቢሮ አድራሻ

በመላው ቴክሳስ ላሉ ደንበኞችን የህግ ማማከር እና አገልግሎት እንሰጣለን።

 

8150 North Central Expressway, Suite 1000
Dallas, TX, 75206

Dallas

አቅጣጫ
 
አቅጣጫ

1504 Ransom Street Pflugerville, TX, 78660

Austin